ግዮን መደበኛ ቁጠባ ማህበሩ ከሚሠጣቸው የቁጠባ አማራጮች ዋነኛው ሲሆን ማንኛውም የህብረት ስራ ማህበሩ አባል የሆነ በየዕለቱ ሃምሳ (50) ብር ወይም ወርሀዊ አንድ ሺ አምስት መቶ ብር (1500) የሚቆጥበው የአባልነት ቁጠባ ነው፡፡
በማህበሩ የብድር መመሪያ መሠረት አባሉ ሳያቋርት ለተከታታይ ስድስት (6) ወራት ከቆጠብ የቆጠባውን 3(ሶስት)እጥፍ በ6 በመቶ የወለድ ምጣኔ የብድር ተጠቃሚ ይሆናል ፡፡
የቁጠባ ሒሳብ እንደብድር ዋስትና ያገለግላል ፡፡
ከተናጥል ወይም አንድነት ዋስትና በቀር የቋሚ ንብረት ዋስትና አይኖረውም ፡፡
ምቹ ተንቀሳቃሽ የቁጠባ ሂሳብ አንድ የማህበሩ አባል ከመደበኛ የቁጠባ ሂሳብ በተጨማሪነት የሚከፍተው የሂሳብ ደብተር ሲሆን በየትኛም ግዜ እና ቦታ ወጪ ገቢ ለማድረግ የሚጠቀሙት የሂሳብ አማራጭ ነው።
በዓመት የ9% በመቶ የወለድ ምጣኔ ይታሰብበታል
በየቀኑ ታሳቢ የሚሆን የወለድ መጣኔ ያለው ነው ፡፡
አባሉ ለሚሳተፍባቸው የብድር አማራጮች እንደ እንቅስቃሴ ማሳያ ይታያል ፡፡
በየትኛውም የማህበሩ ቅርጫፎች የገቢ እና ወጪ እንቅስቃሴ ማድረግ ያስችላል ፡፡
በማህበሩ የብድር መመሪያ መሠረት የብድር ተጠቃሚ ይሆናል ፡፡
የማህበሩን ህግ እና መመሪያ የሚያከብር ፡፡
የብሄራዊ መታወቂያ ፋይዳ ፤ ፓስፖርት ፤ የንግድ ፍቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ቁጥር ማቅረብ ፡፡
የግዮን መደበኛ የቁጠባ ሂሳብ መክፈት ፡፡
ሁለት ጉርድ ፎቶ፡፡
ማህበሩ ከሚሰጣቻው የቁጠባ ሂሳቦች አንዱ ሲሆን እድማቸው ከ 40 ዓመት በላይ ለሆኑ የማህበሩ አባላት የሚከፍቱት የቁጠባ ሂሳብ ነው፡፡
በዓመት በ12 በመቶ የወለድ ምጣኔ ይታሰባል፡፡
የቁጠባ ሂሳብ እንደ ብድር ዋስትና ያገለግላል፡፡
በየትኛውም የማህበሩ ቅርንጫፎች የገቢ እና ወጪ እንቅስቃሴ ማደረግ ያስችላል፡፡
የማህበሩን ህግና መመሪያ የሚያከብር::
ከ40 ዓመት በላይ ለሆነ::
የማህበሩ አባል በመሆን የግዮን መደበኛ ሂሳብ መክፈት::
የብሄራዊ መታወቂያ ፋይዳ ፤ ፓስፖርት ፤ የታደሰ መታወቂያ፤ የንግድ ምዝገባ ቁጥር ማቅረብ::
የህፃናት የቁጠባ ሂሳብ የማህበሩ አባላት ለታዳጊ ልጆቻቸው በልዩ የቁጠባ አማራጭ የሚቆጥቡት የማህበሩ የቁጠባ አማራጭ ነው፡፡
የቁጠባ የብር መጠን ከብር 100 ብር ጀምሮ ይሆናል፡፡
በየአመቱ አስር በመቶ (10) ምጣኔ ወለድ ይታሰባል፡፡
የተሻለ ቁጠባ ላደረገ ወላጅ ስጦታ ይደረግለታል፡፡
የማህበሩ የብድር መመሪያ መሠረት የብድር ተጠቃሚ ይሆናል።
የማህበሩን ህግና መመሪያ የሚያከብር::
የወሳኝ ኩነት የውልደት ምስክር ወረቀት ማቅረብ::
የወላጅ (ያሳዳጊ) 2 ጉርድ ፎቶ የልጅ 2 ጉርድ ፎቶ, ከ18 ዓመት በታች ለሆነ::
የማህበሩ አባል በመሆን የግዮን መደበኛ ሂሳብ መክፈት::
የብሄራዊ መታወቂያ ፋይዳ ፤ ፓስፖርት ፤ የታደሰ መታወቂያ፤ የንግድ ምዝገባ ቁጥር ማቅረብ ::