South Ethiopia, Ethiopia

ብድር ለመውሰድ ማሟላት ያለብን ሰነዶች ምንድን ናቸው ?

1. የማህበሩ አባል መሆን ።
2. ናሸናል አይዲ ( የዋስ እና የተበዳሪ ዋና እና 2 ኮፒ ) ።
3. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፣ የዋና ምዝገባ ፍቃድ ፣ የቲን ሰርተፍኬት ኮፒ።
4. ዋስትናው መኪና ከሆነ ኦሪጅናል ሊብሬ እና ኮፒ፣ የኢንሹራንስ ውል የሻንሲ፣ የሞተር ቁጥር የመኪናው ግምት የያዘ ሰንጠረዥ ኮፒ፣ በተጨማሪም ኢንሹራንሱ በባለንብረቱና
በግዮን ስም መሆን አለበት እንዲሁም ( ተቋሙ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ያግዳል )።
5. ዋስትናው ቤት ከሆነ ኦሪጅናል ካርታ እና ኮፒ እንዲሁም ( ተቋሙ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ ያግዳል )።
6. ለቤት ስራ ብድር ከሆነ ኦርጅናል ካርታ እና ፕላን፣ የኢንሹራንስ ውል እንዲሁም የግንባታ ፍቃድ።
7. በኮንትራክተር ስራ ላይ ላሉ የመስሪያ ቦታው ኪራይ ከሆነ የቤት ኪራይ ውል ኮፒ እና የስራ ኮንትርት ውል ኮፒ የቤት ኪራይ ውል ኮፒ እና የስራ ኮንትራት ውል ኮፒ ።
8. የምቹ ተንቀሳቃሽ ገቢ እና ወጪ የሚያሳይ እስቴትመንት ።
9. ከገቢዎች ግብር የተከፈለበት ደረስኝና ክሊራንስ ።
10. ለመኪና መግዣ ብድር ከሆነ የዋጋ ማቅረቢያ ( ፕሮፎርማ ) ።
11. የጋብቻ ሁኔታ የዋስ እና የተበዳሪ ( ያላገባ ሰርተፍኬት ወይም የጋብቻ ሰርተፍኬት ) ኮፒ እና የቲን ሰርተፍኬት ።
12. (4) ጉርድ ፎቶ ግራፍ ።
13. ተበዳሪው እና ዋስ እንዲሁም የሁለቱም የትዳር አጋሮች ካሉ የተቋሙ ውሎች ላይ መፈረም ይኖርባቸዋል ።
14. የማህበሩን እጣ ከዝቅተኛ ጀምሮ እንደየፍላጎቶ መግዛት ።
15. የማህበሩን ዕለታዊ ወይም ወራዊ ቁጠባ መቆጠብ ።

Didn't find your answer? Contact us directly for further assistance.